arrow_back
LFEBridge
DONATE

close


በባእድ አገር መሰደዳችን ካስተማረን ቁምነገር መካከል፣ አብሮነት፣ ተሳስቦና ተረዳድቶ መኖርን ነው። መቼም ቢሆን በስደት ላይ በታረዝን ጊዜ ያለበሱንን፣ በተራብን ጊዜ ያበሉንን፣ በተቸገርን ጊዜ የደረሱልንን፣ ተስፋ በቆረጥን ጊዜ ያጽናኑንን፣ መጠጊያ በሌለን ጊዜ በራቸውን የከፈቱልንን የመከራ ጊዜ ወገኖቻችንን መርሳት አይቻለንም። በመላው አለም ተበትናችሁ ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እና ኤርታራውያን ወገኖች ሆይ፤ በተለይ በኬንያ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የስደት ጣቢያዎች፣ በዋልዳ፣ በካኩማ፣ በመርሳቤት፣ በቲካ፣ በኢፎ፣ በደደብ ካምፖች በነበራችሁበት ጊዜያት፤ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ለተቸገረ ሁሉ በመድረስ ጊዜውንና ገንዘቡን እንዲሁም የፍቅር ልቡን እያፈሰሰ፣ ያንን ክፉ ዘመን ከግዚያብሄር እንደምንሻገር እየነገረ፣ እያጽናና፣ እንደታላቅ ወንድም፣ እንደ አባት፣ እንደ እግዚያብሄር መልክተኛ ሆኖ የመከረንን እና የረዳንን ጋሽ ውብሸት መንገሻን መቼም ቢሆን አንዘነጋውም። ይህ ወንድም ናይሮቢ ከተማ ውስጥ ተከራይቶ የሚኖርበትን ቤት ክፍት አድርጎ መጠጊያ የሌላቸውን ወገኖቻችንን እያኖረ፣ ለአስቤዛ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ እየሰጠ፣ ለትራንስፖርት የሚሆን ገንዘብ እያዘጋጀ፣ ሌላው ቀርቶ ቤት እየተከራየ ብዙዎችን እንዳስጠለለ እናውቃለን። በተለይ የስደት ዘመናቸውን ጨርሰው ለሚሄዱ ወገኖች አለኝታ እንደነበረ እናስታውሳለን። ቀደም ብለን በጠቀስናቸው የስደት ጣቢያዎች፤ ለእህቶቻችን የንጽህና መጠበቂያ፣ ነጠላ ጫማ፣ ለወንድሞች ሱሪና ከኔቴራ እንዲሁም ጫማ እየገዛ፤ እንዲሁም መልክት እየተቀበለ፣ ፖስታ እየላከ፣ የጉልምስና ዘመኑን በሙሉ ስደተኛውን በማገልገል ማሳለፉን ሁላችንም የምንመሰክረው ጉዳይ ነው። ጋሽ ውብሸት በዚህ ብቻ ሳይገታ ለሰው ልጆች የሚያስፈልገውን ስጋዊና ምድራዊ ቁሳቁስ ከማቅረብ ባሻገር ነፍሳችን የሚያስፈልጋትን መንፈሳዊ ምግብ በማዘጋጀት ብዙዎቻችንን አገልግሏል። በመሆኑም ጋሽ ውበሸት ያለውን ሁሉ አሟጦ ሲያገለግለን ለመጦርያው የሚሆነው ተቀማጭ ገንዘብ ለእሱና ለቤተስቡ ማረፊያ የሚሆን መኖርያ ቤት ሳያዘጋጅ ይደክም እንደነበር ስንቶቻችን እናውቃለን? ወንድማችን የግል ቤት ሳይኖረው ከባለቤቱና ከአምስት ልጆቹጋ በመሆን የጡረታ መውጫ ጊዜውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። እኛም ይህንን ጉዳይ በሰማን ጊዜ በጣም ከማዘናችን በላይ ለምን ሁላችንም ያለንን በማሰባሰብ፣ የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ያለብንን የፍቅር እዳ ለመክፈል አንነሳም ብለን ከተመካከርን በኋላ የወንድማችን ፈቃድ ስናገኝ፣ በተለያዩ ሀገራት ለምትኖሩ ለእናንተ ለወዳጆቹ፣ይህን የአርዳታ ጥሪ ለማቅረብ በቅተናል። በመሆኑም ወንድማችን አይዞህ የሚሉትን ወገኖቹን የሚፈልግበት ሰአት ላይ ስለሆነ እድሉ ሳያመልጠን ሁላችንም በልግስና እንድንሰጥ በአክብሮት እንጠይቃችዃለን። አእግዚአብሔር ይባርካችሁ። ሊንኩን በኬንያ ከተማ ስም ባለ በማናቸውም የቫይበርና የዋትሳኣፕ ግሩፕ ሼር በማድረግ ለሚያቁት ሁሉ እንዲዳረስ እናድርግ። "ስደት ያስተሳሰረንንና ያሳለፍነውን የፍቅር ጊዜ የምንረሳው አይደለም" ፈቃደኛ አስተባባሪዎች ዘነበ ይገዙ ከካልጋሪ ጥሩወርቅ ደሳለኝ፟ ፟፟ ከካልጋሪ ወሰን ብርሃኔ ከኤድመንተን ማናዬ በቀለ ከኦትዎ በለጡ አባተ ከካልጋሪ አማረ አልጊኤ ከኦትዎ መጋቢ ፍቃዱ ደገፉ ከኤድመንተን




Artículos relacionados